MONEY & GOVERNMENT BENEFITS

ERI-ETHIO SOLIDARITY FUND: APPLY NOW!

English form: https://www.surveymonkey.com/r/977JX5W
አማርኛቅፅይህንንይጫኑ: https://www.surveymonkey.com/r/eriethioamharic
ብትግርኛንከተንብብኣብዚጥውቕ: https://www.surveymonkey.com/r/eriethiotigrinya
Gey Sinanle Edew Dedqu: https://www.surveymonkey.com/r/eriethioharari
اضغط هنا للتطبيق باللغة العربية: https://www.surveymonkey.com/r/eriethioarabic



Canada Emergency Response Benefit (CERB).
March 25, 2020 - Ottawa, Ontario - Department of Finance Canada


Taxi/Uber/Lyft Driver Benefits - Frequently Asked Questions


Last Updated: March 25, 2020

ለኮቪድ-19 ከኦንታሪዮ መንግሥት ቢሮ የተሰጠ ምላሽ
ፕሪሚይር ፎርድ እና ሚኒትር ፊሊፕ የጠና ክብካቤንና ድጋፍን ለነዋሪው ለመስጠት የሚክከተለውን መግለጫ ሰጥተዋል።
የገንዘብ ሚኒስቴር

------------------------

ሰዎችና ስራዎች

በኮቪድ-19 ምክንያት የትምሕርት ቤቶችና የሕፃናት መዋያዎች መዘጋት ጋር በተያያዘ አንድ ጊዜ ብቻ የሚከፈል እስከ አሥራ ሁለት ዓመት ላለ ልጅ በልጅ $200 ከአሥራ ሁለት ዓመት ጀምሮ ላሉ፣ ልዩ ዕገዛ ለሚፈልጉ ልጆች እና የግል ትምህርት ቤት ተማሪዎችን ጨምሮ $250፣

የአመታዊ የአስተማማኝ ገቢን (GAINS) ለዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ዕጥፍ ማድረግ

የኤሌክትሪክ አገልግሎት ክፍያን ለመኖሪያ ቤቶች፣ ለእርሻዎች፣ ለአነስተኛ ንግድ ተቅቋማት፣ ለ45 ቀናት ድጋፍ ለማድረግ ዝቅተኛ ተመን ብቻ ማስከፈል፣

ለሕክምና ባለሞያዎች፣ ለፖሊስ ኃይሎች፣ ለእሳት አደጋ ሠራተኞች፣ እና ለማረሚያ ቤቶች ዖፊሰሮች የሕፃናት መዋያ ማመቻቸት

ለስድስት ወራት የሚቆይ የኦንታሪዮ ተማሪዎች ዕገዛ ፕሮግራም ብድርንና ወለድን ፋታ በመስጠት ነዋሪዎች ከኪሳቸው ገንዘብ እንዳያጡ መርዳት

-------------------------

የቶሮንቶ ከተማ ነዋሪዎች ቤት ተከራይ ለሆኑ የተዘጋጀ

https://www.toronto.ca/home/media-room/news-releases-media-advisories/?nrkey=4548F3F23C148BE28525853500559827 

March 24, 2020

ዛሬ ከንቲባ ጆን ቶሪ የቶሮንቶን ነዋሪ ኮቪድ-19 ወረርሺኝ ተፅዕኖ ላሳደረባቸው ለመርዳት የሚከተለውን ዕርዳታ እንደሚያገኙ መግለጫ ሰጥተዋል።

በኮቪድ ሳቢያ ስራ ላቆሙት ለተከራዮች እስከ 90 ከመቶ ድረስ የቤት ኪራይ ክፍያቸውን በገቢያቸው ልክ እንዲተመንና

------------------------

ለአከራዮች

https://www.toronto.ca/home/covid-19/economic-support-recovery/economic-support-recovery-for-individuals-families/ 

የኦንታሪዮ ፍርድ ቤት ከቤት ለማፈናቀል፣ ኪራይን እንዲከፍሉ ለማስገደድ፣ ችሎት አይቀመጥም። ምንም እንኳን አከራይ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ቢፅፍም ተከራይ ቤቱን ለቆ ለመውጣት አይገደድም።

Original source: https://news.ontario.ca/mof/en/2020/03/ontarios-action-plan-responding-to-covid-19.html 


Last Updated: March 25, 2020

ለአልበርታ ኗሪዎች በኮቪድ-19 ምክንያት ለተገለሉ የሚሰጥ የገንዘብ ድጋፍ

----------

በኮቪድ-19 ምክንያት ራሳቸውን ከማህበረሰቡ ካገለሉ፣ ወይንም ራሱን ያገለለ ሰው ብቸኛ ተንከባካቢ ከሆኑ እና ለገቢ ማካካሻ ከሌላ ወገን የማይከፈላቸው የአልበርታ ኗሪዎች ለአንድ ጊዜ ብቻ $1146 ይስሰጣቸዋል። ይህ ክፍያ በአፕሪል የሚሰጠው የፌደራል አስቸኳይ ጊዜ እርዳታ Federal Emergency Care Benefit እስኪደርስላችሁ ድረስ የሚሰጥ ነው።

እርስዎ ለፌዴራል ቅጥር ዋስትና federal Employment Insurance benefits, ክፍያ ብቁ ከሆኑ ለዚህ ፕሮግራም እንዲያመለክቱ ይበረታታሉ።

ለዚህ ፕሮግራም ብቁ መሆንዎን በምን ያውቃሉ?

ከዚህ በታች ያለውን የሚያሟሉ ከሆነ ለዚህ ፕሮግራም ብቁ ነዎት

  • በአጠቃላይም ሆነ በከፊል የገቢ መቆም ከገጠምዎት፣ ወይንም ከሌላ ወገን ማካካሻ ያልተሠጠዎት ከሆነ

    • ኮቪድ-19 እንዳለብዎት ተመርምረው ከሆነ

    • በጤና ኃላፊዎች ራስዎን እንዲያገሉ ተደርገው ከሆነ

    • ራሱን ያገለለ ሰው ጥገኛ ከሆኑ

ከዚህ በታች የተዘረዘረው ውስጥ ከሆኑ ለፕሮግራሙ ብቁ አይደሉም።

  • ራስዎን እንዲያገሉ ከመነገርዎት ቀደም ብለው ስራ አቁመው ከሆነ

  • ቤትዎ ሆነው መሥራት የሚችሉ ከሆነ

  • ራስዎን በማግለልዎት ምክንያት የገቢ መቀነስ ካልገጠመዎት

  • ሌሎች ገቢዎችን እያገኙ ከሆነ ለምስሌ የመስሪያ ቤት ጥቅማ ጥቅሞችን የሚያገኙ ከሆነ

    • የሕመም የሥራ ዕረፍት ፈቃድ ክፍያ

    • የፌደራል ቅጥር ዋስትና ክፍያ (EI) ጥቅማ ጥቅሞች

  • በኮቪዲ ምክንያት ራሱን ያገለለን ሳይሆን በሌላ የሕመም ምክንያቶች በቤት ሆነው ሌላን ሰው የሚንከባከቡ ከሆነ

  • ከአልበርታ ውጭ የሚኖሩ ከሆነ

ለዚህ ፕሮግራም ብቁ ካልሆኑ ሌሎች ድጋዎች ከዚህ ያገኛሉ።

እንዴት ያመለክታሉ?

ለተገለሉ አስቸኳይ የዕርዳታ ሲስተም MyAlberta Digital ID (MADI) ይመዝገቡና ቅፆቹን ይሙሉ።

  • MyAlberta Digital ID (MADI) አካውንት ከሌለዎች ቅፁን በመሙላት ሒደት ላይ ሳሉ ያገኛሉ።

  • በሒደቱ የአልበርታ የመጃ ፈቃድ፣ ወይንም የመታወቂያ ቁጥር ያስፈልግዎታል።

  • ቅፁን ለመሙላት በፖስታ የሚመጣውን ማረጋገጫ ኮድ እስኪመጣ 10 ቀናት መጠበቅ የለብዎትም።

ቅፁን ለመሙላት እርዳታ ካስፈለገዎት በዚህ ስልክ ቁጥር (310-4455) መደወል ይችላሉ። ይህ ቁጥር ሰባቱንም ቀን ከ8 am እስከ 8 pm. ክፍት ነው። ምናልባት ስልኩ ብዙ ደንበኞችን እያስተናገደ ሊሆን ስለሚችል እባክዎትን በትዕግስት ይጠብቁ

ካመለከቱ በኋላ

ማመልከቻውን ካስገቡ በኋላ የማረጋገጫ ኢሜይል ከነ ማጣቀሽሻ ቁጥሩ ይላክልዎታል። የማጣቀሻ ቁጥሩ ለወደፊትም የሚጠቅምዎት ነው።

ማመልከቻዎ ተቀባይነትን ካገኘ ከ24 እስከ 48 ሰዓት ውስጥ፡በኢ ትራንስፈር አንድ ጊዜ ብቻ የሚከፈል $1146 ይደርስዎታል

Original source: https://www.alberta.ca/emergency-isolation-support.aspx?fbclid=IwAR3Moglmp4rlc0h9npAynOxxs8awEuvx_4XGvj1NzrHWjntGIeBA5iZ4xfA 


LAST UPDATED MARCH 30, 2020
Powered by Webnode
Create your website for free! This website was made with Webnode. Create your own for free today! Get started